የቴክኖሎጂ ግሩፑ ሴት ሠራተኞች በሩጫ ውድድር ተሳተፉ
መጋቢት 1 ቀን 2006 ዓ.ም.
የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎች ሴት ሠራተኞች የተካፈሉበት የ2006 ዓ.ም. የጐዳና ላይ የሩጫ ውድድር የካቲት 30 ቀን 2006 ዓ.ም. ተካሄደ፡፡
በየዓመቱ በሚካሄደው በዚህ ውድድር ላይ 150 ሠራተኞች የተካፈሉ ሲሆን የቴክኖሎጂ ግሩፑን ሠራተኞች በማበረታታት ወደ ሩጫ ማስጀመሪያ ስፍራ ሽኝት ያደረጉት የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር ዶ/ር አረጋ ይርዳው ሲሆኑ፤ ለተወዳዳሪዎች የማበረታቻ ንግግር አድርገዋል፡፡ ውድድሩ ከመገናኛ ዳያስፖራ አደባባይ ጀምሮ 5 ኪሎ ሜትር ሸፍኖ በዚያው አደባባይ ተጠናቅቋል፡፡
![]() |
![]() |
የሩጫ ውድድሩ ተሳታፊዎች በከፊል |