አንሊሚትድ ፓኬጂንግ ኃ.የተ.የግ.ማኀበር 25ኛው የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ አባል ሆነ
ሚያዝያ 3 ቀን 2009 ዓ.ም
• የሥራ አመራር አባላቱም ትውውቅ አድርገዋል
![]() |
ዶ/ር አረጋ ይርዳው የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር በትውውቅ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የሥራ መመሪያ ሲሰጡ |
በመቻሬ ኮርፓሬት ሴንተር የሚገኙ የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎች ሠራተኞች እንዲሁም የሬይንቦ የመኪና ኪራይና የጉብኝት አገልግሎት እና የአዲስ ሆም ዴፖ ኩባንያዎች ሠራተኞችን ጨምሮ መጋቢት 22 ቀን 2009 ዓ.ም በመቻሬ ኮርፖሬት ሴንተር በተደረገው ወርሃዊ የሠራተኞች ስብሰባ ፕሮግራም ላይ የአንሊሚትድ ፓኬጂንግ ኃ.የተ.የግ.ማኀበር ሥራ አመራር አባላትና የኩባንያው የሠራተኛ ማህበር ሊቀመንበር በመገኘት ትውውቅ ተደርጓል፡፡ በዚሁ ጊዜም የአንሊሚትድ ፓኬጂንግ ኃ.የተ.የግ.ማኀበር ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አስፋው ከበደ ኩባንያው የተሰማራበትን የሥራ ዘርፍ አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ የኩባንያው መለያ አርማም /Logo/ በተሰብሳቢዎቹ እንዲታወቅ ተደርጓል፡፡
የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር ዶ/ር አረጋ ይርዳው በዚሁ የትውውቅ ሥነ-ሥርዓት ላይ እንደገለጹት የተደረገው ትውውቅ ለኩባንያዎቹ የኀብረት ሥራ ጠቃሚ መሆኑን ገልጸው፣ ለኩባንያው ለወደፊት ሥራ ስኬታማነት የሚረዱ የሥራ መመሪያዎችን ሰጥተዋል፡፡
በቅርቡ 25ኛው የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎች አባል ሆኖ የተቀላቀለው አንሊሚትድ ፓኬጂንግ ዋና የሥራ ቦታው ደብረ ዘይት ሲሆን ኩባንያው ለተለያዩ የምርት ውጤቶች ማሸጊያ /Packaging/ የሚያገለግሉ ምርቶችን በማቅረብ የሚታወቅ ነው፡፡
![]() |
የኩባንያው የሥራ አመራር አባላት እና የኩባንያው አርማ /Logo/ |