ሬይንቦ ኤክስክሉሲቭ የመኪና ኪራይና አስጎብኝ አገልግሎት ኩባንያ የከተማ ውስጥ የማስጉብኘት ሥራውን ጀመረ
ኅዳር 15 ቀን 2008 ዓ.ም
![]() |
ሬይንቦ ተጓዦችን ወደ ሶደሬ ሲያንቀሳቅስ |
ሬይንቦ ኤክስክሉሲቭ የመኪና ኪራይና አስጎብኚ አገልግሎት ኃ.የተ.የግ ማህበር በሃገር ውስጥ ጉብኝት በርካታ የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ሠራተኞችና ቤተሰቦችን በመያዝ የመጀመሪያውን ሶደሬ መዝናኛ ጉዞ ፕሮግራም ህዳር 5 ቀን 2008 ዓ.ም በማድረግ ጐብኝዎችን አዝናንቷል፡፡
ሬይንቦ በከተማ ውስጥ በማካሄድ የጀመረውን ፕሮግራም በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኙ የቱሪስት መስህቦችንና የመዝናኛ ሥፍራዎችን ተደራሽ በማድረግ እያስፋፋ ሲሆን ይህ ፕሮግራም ወደፊት ያለማቋረጥ የሚካሄድ መሆኑን እና በቀጣይ በአዲስ አበባ ከተማ ከከተማዋ በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኙ የቱሪስት መስህቦችን እና የመዝናኛ ሥፍራዎችን ወደ ሃዋሳና ሌሎች ቦታዎች የሚደረጉ ልዩ ልዩ የጉዞ ኘሮግራሞችን ያዘጋጀ ስለሆነ በቡድንም ሆነ በግል ለመጓዝ ለሚፈልጉ ከሰፊ ሙያዊ መግለጫ ጋር ለማስተናገድ መዘጋጀቱን ከኩባንያው ኃላፊዎች መረዳት ተችሏል፡፡
![]() |
የተጓዦች የቡድን ፎቶ |