የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎች ሠራተኞች የተሣትፉበት የታላቁ ሩጫ የ10 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ውድድር ተካሄደ
ኅዳር 16 ቀን 2008 ዓ.ም
![]() |
ለ15ኛ ጊዜ የተካሄደው ታላቁ ሩጫ ላይ ተሣታፊ የነበሩት ሠራተኞች በከፊል |
በአዲስ አበባ ከተማ የተካሄደው ታላቁ ሩጫ ከ40,000 ሕዝብ በላይ የተሣተፈበት ሞቅና ደመቅ ያለ መነሻና መድረሻውን በመስቀል አደባባይ ያደረገ ሩጫ እሁድ ህዳር 12 ቀን 2008 ዓ.ም ተካሄደ፡፡
በዚህ ታላቁ ሩጫ የ10ሺህ ኪ.ሜትር የጐዳና ላይ ውድድር ሲካሄድ ከኩባንያዎቻችን የተውጣጡ በርካታ ሠራተኞች የተሳተፉ ሲሆን መነሻና መድረሻው መስቀል አደባባይ ሆኖ ውድድሩ ከመጀመሩ በፊት በሬይንቦ ኤክስክሉሲቭ የመኪና አስጐብኝ አገልግሎት ኩባንያ ቅጥር ግቢ በመገኘት የማስታወሻ ፎቶግራፍ ተነስተዋል፡፡
ታላቁ ሩጫ የጎዳና ላይ ውድድር በርካታ የቴክኖሎጂ ግሩፑ ሠራተኞች በየጊዜው የሚስብና ቁጥራቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣ ተወዳዳሪዎችን ያፈራ ከመሆኑም በላይ በህብረተሰቡ ዘንድ አዝናኝ የስፖርት ዓይነት በመሆን ላይ ይገኛል፡፡
![]() |
![]() |